የዘፀዓት ወጣቶች

የዘፀአት ወጣቶች (YM4TN)

ዘፀአት ዩዝ የዘፀአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ነው። ይኸውም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ እስከ 35 ዕድሜ ክልል ያሉ ወጣቶችን ያካትታል። የአገልግሎቱ ግብ ወጣቶቻችንን ዓለምን የሚለውጡ አድርጎ ማስታጠቅ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከተማዎች እና በሀገራት ላይ ለውጥ ለማምጣት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እናስተናግዳለን።

ተልዕኮ

ተልዕኮአችን ነፍሳትን ወደ እግዚአብሔር መንግስት በመማረክ ት/ቤቶችን፣ ከተማዎችንና ሀገራትን ደቀ መዝሙር በማድረግ ተሃድሶ ማምጣት ነው። ይህንን ለውጥ ለማምጣት ትምህርት ቤቶች እና ከተሞች ላይ እንዲሁም ሀገራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን።

ትምህርት ቤቶች

ትምህርት ቤቶች በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳላቸው እናምናለን። መንፈስ ቅዱስ ሊመጣ ላለው የመጨረሻው ዘመን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ዋና ማዕከል እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችን እያነቃቃ ነው።

ከተሞች

መንግስታት የበላይ ለሆነው የእግዚአብሔር መንግስት እንዲገዙ እንሰራለን። የአሮን በትር የአስማተኞችን በትር እንደዋጠች የዚህ ዓለም ስርዓቶች በዘላለማዊው ስርዓት መዋጥ ይገባቸዋል። እግዚአብሔር ስርዓቶችን የመንግስቱ እሴቶች ወደሆኑት ወደ ሰላም፣ ደስታ እና በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ እየመለሰ ነው።

ሁለተኛና ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት

የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል በመስበክ ትምህርት ቤቶች ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማምጣት እንሰራለን። የትምህርት ቤታቸውን ባህል ወደ እግዚአብሔር መንግስታዊ ባህል መቀየር እንዲችሉ ክርስቲያን ወጣቶችን የማስታጠቅ ስራም እንሰራለን። ትምህርት ቤቶች በእግዚአብሔር መንግስት የጽድቅ ሞገድ ሊመቱ ተዘጋጅተዋል። ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሊመጣ ላለው ሪቫይቫል ቀዳሚ የጉብኝት ስፍራ ሆነው የማየት ትልቅ ናፍቆት አለን።

ባለሙያዎች

ፕሮፌሽናልስ የከተማን ባህል ለመቀየር የምንሰራበት የ ዘፀአት ዩዝ አንዱ ክንፍ ነው። ከከፍተኛ ትምህርት የተመረቁ ወጣቶቻችን በእግዚአብሔር መንግስት እሴቶች ታጥቀው በገቡበት ሁሉ ብርሀንና ጨው እንዲሆኑ ወደ ስርዓቶች ይላካሉ።

የወጣቶች መርሀ-ግብሮች

ፋየር ናይት (Fire Night)

ይሄ ወጣቶች የተጽዕኖ አድማሳቸውን እንዲያውቁና በተጠሩበት የህይወት ዘርፍ ብርሃን እና ጨው እንዲሆኑ ለማስታጠቅ በሁለት ወር አንዴ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው። የህይወት ተሞክሮአቸውን የሚያካፍሉ ተጋባዥ ተናጋሪዎች ይኖራሉ። እንዲሁም በዕለቱ በሚነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የመድረክ ውይይት ይደረጋል። ዝግጅቱ ምን አይነት እንደሆነ የተሻለ መረዳት እንዲኖርዎ የእነዚህን ምሽቶች ዝግጅት እንዲሳተፉ እንጋብዝዎታለን፤ በእርግጥም "fire" እንደሆነ ይመሰክራሉ።

የኪነጥበብ ምሽት

የሁሉም ኪነጥበብ ዓላማ የእግዚአብሔርን ውበትና መልካምነት መግለጥ ነው። የኪነጥበብ ፈጣሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የጨለማው ዓለም በኪነጥበብና በመዝናኛው ዘርፍ ላይ እንዲሰለጥን አደረግን። የኪነጥበብ ምሽት በሶስት ወር አንዴ የሚደረግ ሲሆን የእግዚአብሔርን መልካምነት በተለያዩ የጥበብ ስራዎች እናከብራለን። ወጣቶቻችን በተሰጣቸው ተሰጥኦ እና ብቃት እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ይበረታታሉ። ግጥሞች፣ መዝሙሮች፣ ራፕ፣ መነባንብ፣ የመድረክ ላይ ትዕይንቶች እና የመሳሰሉት ከዝግጅቱ ይዘቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በድጋሚ ኪነጥበብ እንዴት እግዚአብሔርን እንደሚያመልክ መጥተው እንዲያዩ እንጋብዝዎታለን።

ወርሃ ወንጌል

ሁለት ታላላቅ በዓላት (ልደትና ትንሳኤ) የሚከበርባቸውን ሁለት ወራት ለወንጌል ለይተናቸዋል። ምንም እንኳን ወንጌልን ዓመቱን ሙሉ ብንሰራም፣ ሁለቱ የወንጌል ወራት ወንጌልን በጋለ፣ ኃይለኛ እና ፈጠራ በታከለበት አቀራረብ ላልዳኑት ለመናገር የተለዩ ናቸው። ይህንንም ለማሳካት የጸሎት የወንጌል ስርጭት፣ የሚዲያ የወንጌል ስርጭት፣ የአገልግሎት የወንጌል ስርጭት፣ የት/ቤትና የከተማ ወንጌል ስርጭቶችን እንጠቀማለን።

የክረምት ካምፖች

ክረምት ለወጣቶቻችን እንደ መስፈንጠሪያ ሰሌዳ ነው። በእግዚአብሔርን ቃል እና በመገኘቱ እየተሞላን የምንዘጋጅበት የዝግጅት ወቅት ነው። ለእግዚአብሔር ስራ እንታጠቃለን፤ ኃይልንም እንሞላለን። በክረምቱ የምናደርጋቸው የተለያዩ ተከታታይ ፕሮጀክቶች አሉ

የሆሎ አገልግሎት

የሆሎ አገልግሎት ለሁሉም ክርስቲያኖች መቀደስ እና መለወጥ የሚያግዝ የትምህርት እና የፀሎት አገልግሎት ነው ፡፡ የወንጌልን እውነት ሙሉ በሙሉ ተቀብለው ከክርስቶስ ጋራ ወዳልተባበሩ የአማኝ ልብ ክፍሎች በማድረስና ማንኛውንም በህይወታችን ያሉ መራራ የህይወት ስሮችን በመንፈስቅዱስ ምሪት በማግኘት የክርስቶስ መስቀል ላይ የማኖር አገልግሎት ነው። ስለዚህም ይቅር በማለት ከውሸቶችን እና ከህይወት ጉዳት ጠባሳዎች በመዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋር እውነተኛ የቅርብ ግንኙነት እንዲኖር መልካም ከባቢን ይፈጥራል፡፡

አዌክኒንግ ኮንፈረንስ

እግዚአብሔር ይህንን መገለጥ የሰጠን ስለ ታዳጊ ወጣቶች ያለውን ልብ እንዲያሳየን በፊቱ እየጸለይን በነበረበት ጊዜ ነበር። ከልጅነታችን ጀምሮ ሊመጣ ስላለው ሪቫይቫል ብዙ ሰምተናል። ነገር ግን መቼ እና እንዴት እንደሚሆን አናውቅም ነበር። የተስፋ ቃሎቹ እውነት አይደሉም ? ከሰማይ ለእኛ ለመጣው መገለጥና ትንቢት መነሻ የሆነው ይሄ ነበር። የፍጥረታት ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለን “እናንተ እየጠበቃችሁት ያለው ሪቫይቫል ራሱ እናንተን እየጠበቀ ነው።” ይህ አስደንጋጭ ነው። እኛም “ይሄ እንዴት እውነት ሊሆን ይችላል?” ብለን ነበር። ምናልባት እግዚአብሔር ቀጣይ ሪቫይቫሊስቶችን እየፈለገ ይሆናል። እኛም አሁን የቀጣዩን አዲስ የሪቫይቫል ትውልድ በማስነሳት ስራ ውስጥ ገብተናል። አዌክኒንግ ኮንፈረንስ እነዚህን ሪቫይቫሊስቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ በእግዚአብሔር ቃል እና በእግዚአብሔር መንፈስ ለማስታጠቅ የተዘጋጀ ነው።

የአገልግሎት ት/ቤት

በታሪክ እንደምናየው እግዚአብሔር ክብሩን ልኮ ዓለምን ከመጎብኘቱ በፊት ክብሩን መሸከም የሚችሉ እና በእነርሱ በኩል የሚጎበኝባቸውን ሰዎች ይልካል። ዓለምን ከመጎብኘቱ በፊት እነዚህን የሚላኩ ሰዎች አስቀድሞ ይጠራቸዋል። ክብሩን ተሸክመው ወደ ዓለም ለመሄድ የሚናፍቁ ሰዎችን ይፈልጋል። የእግዚአብሔርን ኃይለኛ እንቅስቃሴ ከማየታችን በፊት የእግዚአብሔር ዕቃ የሚሆን ትውልድ ቀድሞ መምጣት አለበት። እግዚአብሔር የሚልከውን ትውልድ እየፈለገ ነው።

“የእግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው፥” ሉቃስ 9፥2

የተልዕኮ ት/ቤት የእግዚአብሔርን መልእክት ወደ ዓለም ለማድረስ ህይወታቸውን የሰጡ ወጣት ሚስዮናውያንን ማስታጠቅን ዓላማው ያደረገ የአገልግሎት ክፍል ነው። ወጣት ሚስዮናውያን በቃሉና በመንፈሱ በኃይል በሞልተው እንዲታጠቁ የሚያስችል መድረክ ነው። ባሉበት ቦታ ሁሉ ታላቁን ተልዕኮ ለመፈጸም የሚያስችሉ መሰረታዊ መሳሪያዎችን ያቀርባል

አ.ወ.ጉ - አመታዊ የወጣቶች ጉባኤ

የአ.ወ.ጉ ታሪካዊ ዳራ

አመታዊ የወጣቶች ጉባኤ በዘፀአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት በየዓመቱ የሚደረግ ፕሮግራም ነው። ጉባኤው በየዓመቱ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ በሀበሻ ካላንደር በዓመቱ መጨረሻ ላይ ይደረጋል። አመታዊ የወጣቶች ጉባኤ ከረጅም ጊዜ በፊት በቀደሙ የዘፀአት የወጣት መሪዎች የተጸነሰ ነው።\ ብቻችንን በሀገሪቱ ላይ ልዩነት ማምጣት እንደማንችል በመረዳት ለአንድነት ትልቅ ጥማት ነበረ። ሀገር አቀፍ ብሎም ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለማሸነፍ እና ወጣቱን ለእግዚአብሔር መንግስት ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ሀገርን መሰረት ያደረገ የክርስቲያን ወጣቶች አንድነት ወሳኝ ነው።

ራዕይ

የዚህን ዘመን ወጣት ትውልድ ለጊዜው በሆነ የእግዚአብሔር አጀንዳ መድረስ።

ግብ

ከመነሻው ጀምሮ የአመታዊ የወጣቶች ጉባኤ ግብ በዓለም ላይ ያሉ ወጣቶችን በአንድ ተልዕኮ ስር በአንድነት እንዲያያዙ ማድረግ የሚያስችል መድረክ መፍጠር ነው፤ የጊዜው አጀንዳ ምን እንደሆነ በመረዳት ከአንድ ጀነራል ስር እንዳሉ ወታደሮች እጅ ለእጅ እንዲያያዙ የሚያደርግ። ሌላው ግልጽ የሆነው ግቡ እግዚአብሔር ትውልዱን እንደ አንድ ሰው በልቡ ያለውን የጊዜውን አጀንዳ የሚናገርበት መድረክ ነው።

ታሪክ

የአመታዊ የወጣቶት ጉባኤ ( AYS) ታሪክ ላለፉት 5 የቆየ ነው፤ ከ2015 እስከ 2019 እ.ኤ.አ። እያንዳንዱ አ.ወ.ጉ (AYS) ወጣቱንና የእግዚአብሔርን የጊዜው አጀንዳ የደረሰ የተለየ ዘውግ ነበረው።

  • AYS|2015, ዘውግ: የቀጠሮ ትውልድ
  • AYS | 2016, ዘውግ: ታላቅ ሰራዊት
  • AYS | 2017, ዘውግ: ወደፊት መገስገስ
  • AYS | 2018, ዘውግ: የእሳት ችቦ
  • AYS | 2019, ዘውግ: ጎርፍ

ይመዝገቡ

አዳዲስ መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርስዎ የኢሜይል አድራሻዎትን እዚህ ጋር በማስገባት ይመዝገቡ