ጦማሮች
ያጋሩ

የምንሰማውን ደምፅ እንምረጥ

Published 3 years ago by Zetseat Church

ዙ ጊዜ ስለእኛ እና ስላለንበት ሁኔታ የሚያወሩ ብዙ ድምፆችንእ ንሰማለን። ውስጣችን፣ቤተሰቦቻችን፣ጓደኞቻችን፣የተለያዪ ሰዎችና ሁኔታዎች ስለ እኛ ብዙ ነገር ይላሉ። የተለያዪ ድምፃች ከተለያዩ ቦታዎችና ምንጮች ወደ እኛ ይመጣሉ። እነዚህ የምንሰማቸውና ሰምተን የምንቀበላቸው ድምፃች የሕይወታችንን አቅጣጫ የመወሰን ትልቅ ይል አላቸው። ስለዚህም የምንሰማቸውን ድምፆች ሁሉ ተቀብሎ ማስተናገድ ወደ ተወዛገበ እና አቅጣጫው ወደጠፋ ሕይወት ይወስዱናል። እናም ወደ ጆሮአችን የሚመጡትን ድምፃች መርጠን መስማትና ምንጫቸውን ማጣራት ይኖርብናል። ስለእኛ እና ስላለንበት ሁኔታ የመናገር ሙሉ መብት ያለው ፈጣሪያችን ነውና ሌሎች ድምፆችን ፀጥ በማሰኘትና በመተው እርሱ ስለ እኛ ያለውን ድምፅ ደጋግመን እንስማ፤በሕይወታችንም ላይ እንናገር!!!